የገና በዓል በቅዱስ ላሊበላ በደማቅ ስነ ስርአት እየተከበረ ነው

AMN – ታኀሣሥ 29/2017 ዓ.ም

በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በቤዛ ኩሉ የዝማሜ ስነ-ስርአት እየተከበረ ነው።

በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ የሚከወነው የቤዛ ኩሉ የዝማሜ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቃ-ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስን ጨምሮ ሌሎች ብጹዓን ሊቀ ጳጳሳት፣ የክብር እንግዶች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶችና በርካታ ቁጥር ያለው ምእመናን እየተሳተፉ ነው።

ከትላንት ምሽት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ የሚያበስረው የዝማሜ፣ መዝሙርና የቅዳሴ ስነ-ስርአት ተጠናቆ አሁን ላይ የቤዛ ኩሉ ስነ-ስርዓት እየተከወነ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።

በየአመቱ በታላቅ ኃይማኖታዊ ስነ-ስረአት በቅዱስ ላሊበላ የሚከበረው የገና በዓል ከኃይማኖታዊ ሥርዓትም ባለፈ በቱሪዝም መዳረሻነቱ ይታወቃል።

+2

All reactions:

1616

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review