የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል

AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ በርካታ ውሳኔዎች እና ወሳኝ አቅጣጫዎች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው ላይ ከፓርቲው አባላት እና አመራሮች በተጨማሪ የጎረቤት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡

በዚህም በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እንዲሁም የእህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከዛሬ ጥር 23 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review