AMN – የካቲት 7/2017 ዓ.ም
እንደ ቅርብ ጎረቤት እና እህት ሀገር ኢትዮጵያ በዚህ የፈተና ጊዜ ከሱዳን ሕዝብ ጋር በአጋርነት ትቆማለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ጋር በመሆን ለሱዳን ሕዝብ የሰብዓዊ ድጋፍ ከፍተኛ ኮንፈረንስ በጋራ በማዘጋጀቷ ደስታ ይሰማታል ብለዋል።
እንደ ቅርብ ጎረቤት እና እህት ሀገር ኢትዮጵያ በዚህ የፈተና ጊዜ ከሱዳን ሕዝብ ጋር በአጋርነት እንደምትቆም አስታውቀዋል።
ሁለቱ ሀገሮቻችን በጥልቅ የተሳሰሩ በትውልዶች የጋራ ትግል፣ የጋራ ምኞት እና ባሕላዊ ቁርኝት የተጋመዱ ናቸው ሲሉም አክለዋል።