AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ልዑካን ቡድናቸዉ ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡
ከንቲባዋ አርባምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቆይታቸው በከተማዋ የተሰሩ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ እና የህዝብ የምክክር መድረክ ላይም እንደሚሳተፉ ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።