AMN-የካቲት 15/2017 ዓ.ም
በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ውይይት ከአዳማ ከተማ ፣ ከምስራቅ ሸዋ እና ከአርሲ ዞኖች የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በአዳማ ከተማ ገልማ አባ ገዳ እየተካሄደ ነው።
የውይይት መድረክ አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሐይሉ ጀልዴ ከሕዝቡ አዳጊ ፋላጎቶች ጋር የተጣጣመ ስራ ለመስራት ውይይቱ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
የምስራቅ ሸዋ ዋና አስተዳደሪ አቶ አባቡ ዋቆ ለውይይት መነሻ የሚሆን የተለያዩ የሕዝብ ጥያቄዎች እና የተሰሩ ስራዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርት እያቀረቡ ነው።
በውይይት መድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ፣ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ልማት አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ የምስራቅ ሸዋ ዋና አስተዳደሪ አቶ አባቡ ዋቆ ፣ የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በዳንኤል መላኩ