AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም
5ኛው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የስራ ቡድን ስብሰባ ዛሬ ጠዋት በስውዘርላንድ ጄኔቫ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣በድርድር መድረኩ በዋና ተደራዳሪነት የድርድር ቡድኑን በመምራት፣ ሀገራችን ለአባልነት ከምንም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጬ፣ አባል ሀገራት የሁለትዮሽ የንግድ ድርድራቸውን ከወዲሁ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ አቅርቢያለሁ ብለዋል::
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ከ19 በላይ ሀገራት የድጋፍ መልእክት አስተላልፈው አበረታተውናል፤ ያሉት ሚኒስትሩ፣ መድረኩ በጥያቄና መልስ መርሃ ግብር እስከምሽት የሚቀጥል እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡