በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርገው ሀገራዊ ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪ አቀረበ

You are currently viewing በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርገው ሀገራዊ ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑ ጥሪ አቀረበ

AMN – መጋቢት 27/2017

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ማካሄድ ጀምሯል።

የምክክር መድረኩ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ እንዳሉት፣ ኮሚሽኑ በእስካሁን ቆይታው በ10 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች በ971 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የአጀንዳ ልየታ ስራ በስኬት አጠናቋል።

በአማራ ክልል ከ263 ወረዳዎች ከ4 ሺህ 500 በላይ ተሳታፊዎች በህዝብ ተመርጠው መመካከር መጀመራቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የሀሳብ ልዩነቶች የፈጠሯቸውን አለመግባባቶች ለመፍታት ከመመካር ውጪ ያሉ አማራጮች ጊዜያዊ ድልን እንጂ ዘላቂ መፍትሔን አያዋልዱም ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ፣ በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርገው ምክክር እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መንገድ በመፍታት አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር እንዲሁም ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የሚደረገው ጥረት በስኬት እንዲቋጭ የተወካዮች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ስለመሆኑም ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review