አዲስ አበባ በመዲናዋ እየተካሄደ ባለው ዓለምዓቀፍ ጉባኤ በሲቪል ምዝገባ እና የፋይዳ ስርዓት ላይ እየሰራች ያለውን ስራ ልምድ አቅርባለች

You are currently viewing አዲስ አበባ በመዲናዋ እየተካሄደ ባለው ዓለምዓቀፍ ጉባኤ በሲቪል ምዝገባ እና የፋይዳ ስርዓት ላይ እየሰራች ያለውን ስራ ልምድ አቅርባለች

AMN- ግንቦት 13/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ እያስተናገደች ባለው ዓለም ዓቀፉ የኤይ ዲ ፎር አፍሪካ (ID4 Africa) 11ኛ ጉባኤ በወሳኝ ኩነት እና በፋይዳ ምዝገባ ቅንጅታዊ ትግበራ ላይ የቅንጅት ልምዷን አቅርባለች።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ የሲቪል ምዝገባ ሽፋንን በማጠናከር ዘርፉን ለመለወጥ የከተማ አስተዳደሩ የወሰደውን እርምጃ፣ ከፋይዳ ስርዓት ጋር ቅንጅት ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ፣ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት እንዲሁም የተገኘውን ውጤት በመድረኩ አካፍለዋል።

በጉባኤው ላይ የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎችን ጨምሮ ከ105 ሀገራት የተውጣጡ ከ2 ሺህ 300 በላይ ተሳታፊዎች በመታደም ላይ ይገኛሉ፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review