የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን የተገልጋይን እንግልት መቀነስ መቻሉን ገለጸ

You are currently viewing የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን የተገልጋይን እንግልት መቀነስ መቻሉን ገለጸ

AMN- ግንቦት 19/2017 ዓ.ም

የስራ ቦታን ምቹ በማድረግ እና አገልግሎቱን ከወረቀት ነፃ በማድረግ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ማዘመኑ የተገልጋይን እንግልት የቀነሰ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለከተማው ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።

አገልግሎቱን ማዘመኑ በተለይም በመሬት አገልግሎት ላይ ሲነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቀነስ እንዳስቻለውም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በቀጣይም በመሬትና መሬት ነክ በሆኑ አገልግሎቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የቢሮውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በሲስተም በማስተሳሰር በትኩረት እንደሚሰራም ነው የገለጸው።

የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ያዳመጠው ቋሚ ኮሚቴው፣ በሪፖርቱ ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በአይናለም አባይነህ እና በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review