ለቀጣይ ሳምንቱ የሰላም ድርድር የዩክሬንን ምላሽ እየጠበቅኩ ነው – ሩሲያ

You are currently viewing ለቀጣይ ሳምንቱ የሰላም ድርድር የዩክሬንን ምላሽ እየጠበቅኩ ነው – ሩሲያ

AMN – ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

ሩሲያ በቀጣይ ሳምንት ሰኞ በኢስታንቡል ሊካሄድ ለታቀደው የሰላም ድርድር የዩክሬንን ምላሽ እየጠበቀች መሆኗን አስታውቃለች።

ሞስኮ ባቀረበችው የሁለተኛ ዙር የፊት ለፊት ድርድር ላይ የረዥም ጊዜ የሰላም ስምምነት ሰነድ

ይዛ እንደምትቀርብ ማስታወቋ በሀገራቱ መካከል ተጨማሪ የልዩነት ነጥብ ሆኗል።

ዩክሬን ሰነዱን አስቀድማ እስካላየች ድረስ ድርድሩ ውጤት አልባ እንደሚሆን መግለጿን ተከትሎ ሩሲያ የሀገሪቱን ጥያቄ “ገንቢ ያልሆነ” በሚል ውድቅ አድርጋዋለች።

ዩክሬን የሰላም ሃሳቦቿን ለሩሲያ እንዳስገባች እና ሞስኮም አፀፋውን እንድትመልስ መጠየቋንም አስታውቃለች።

ከሁለት ሳምንት በፊት በቱርክ ኢስታንቡል የተካሄደው የሀገራቱ ድርድር የጦር እስረኞችን ከመለዋወጥ ባለፈ ለተኩስ አቁም እና ለዘላቂ ሰላም የሚበጅ አይነተኛ መፍትሔ ሳይገኝበት መጠናቀቁ ይታወሲል ሲል አርቲ ዘግቧል።

ከፍተኛ የሆነ የእስረኞች ልውውጥን ከማስከተሉ ውጪ ውጤት አለማስገኘቱን አር ቲ ኢ በዘገባው አስታውሷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review