የተጀመሩ የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የተጀመሩ የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

AMN – ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶሜ አበበ (ዶ/ር) የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናቀቅና ፕሮጀክቶችን ጨርሶ በማውጣት በቀጣይ በጀት ዓመት አዳዲስ የቤት ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር መዘጋጀት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬትና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በቦሌ በሻሌ፣ በቦሌ አራብሳ እና በቦሌ አያት የግንባታ ሳይቶች በመገኘት ቤቶቹን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የማጠናቀቂያ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

አቶሜ አበበ (ዶ/ር) ጉብኝቱ የግንባታ ሳይቶችና ቤቶችን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በመገምገምና የቀሩ ስራዎችን በመለየት ቶሎ የሚጠናቀቁበትን ሁኔታ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውሃ አቅርቦትና የውሃ ፓምፕ በማስገጠም፣ ሊፍቶችን በማስገጠም እና የመብራት አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ ቤቶች ለኑሮ ምቹ እየሆኑ እንደሆነ አዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ አለሙ (ኢ/ር) ገልፀዋል።

ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረውም የመንገድ መሰረት ልማት ዝርጋታ ስራው ልዩ ትኩረት እንደሚያሻው ጠቁመዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review