ሩሲያ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካልተቀበለች አሜሪካ ራሷን ከድርድሩ እንደምታገል አስታወቀች

You are currently viewing ሩሲያ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካልተቀበለች አሜሪካ ራሷን ከድርድሩ እንደምታገል አስታወቀች

AMN – ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

ሩሲያ የተኩስ አቁም ስምምነቱን የማትቀበል ከሆነ አሜሪካ ራሷን ከድርድሩ እንደምታገል አስታውቃለች፡፡

አሜሪካ፣ ሩሲያ የ30 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነቱን የምትገፋ ከሆነ ሀገሪቱ ላይ ማዕቀብ እንደምትጥልም አስጠንቅቃለች፡፡

ትራምፕ በዩክሬን የተኩስ አቁም ጉዳይ ላይ ፑቲን ቁርጥ ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁ የሁለት ሳምንት ቀነ ገደብ ሰጥቻለሁ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ትራምፕ እና ፑቲን ካደረጉት የስልክ ውይይት በኃላ ሩሲያ የስምምነት ሰነድ አለማቅረቧ በአሜሪካ ዘንድ የቁርጠኝነት ማነስ ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡

ክሬምሊን በበኩሉ በመጪው ሰኞ በኢስታንቡል ለሚካሄደው የሰላም ድርድር የዩክሬንን ምላሽ እየጠበቅኩኝ ነው ብሏል፡፡

ዩክሬን ለተጋበዘችበት 2ኛ ዙር የሰላም ድርድር እስካሁን መስል አለመስጠቷንም ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review