በመዲናዋ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ የወንጀል ምጣኔ እንደቀነሰ ተመላከተ

You are currently viewing በመዲናዋ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ የወንጀል ምጣኔ እንደቀነሰ ተመላከተ

AMN – ግንቦት 23/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት 11 ወራት ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከሀገረ ሽማግሌዎች እና ከከተማዋ ነዎሪዎች ጋር እየተወያየ ይገኘል፡፡

የቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለጹት፣ በመዲናዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲሳኩ ሰላምና ፀጥታዉን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረዉ ሲተገበሩ መቆየታቸዉን አንስተዋል፡፡

በተለይም በመዲናዋ ይከሰቱ የነበሩ ወንጀሎችን ለመቀነስ ህብረተሰቡን ባሳተፈ የተጠያቂነት አሰራ መዘረጋት በመቻሉ፣ የወንጀል ምጣኔዉ ከአምናዉ ጋር ሲነፃፀር 43 በመቶ እንዲቀን ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በከተማዋ ሰላም መረጋገጥ ላይ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅረበት እየሰራ የሚገኘዉ የሰላም ሰራዊትን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል በሶስት ዙር ከ32 ሺ በላይ አዳዲስ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲቀላቀሉ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

መዲናዋ የጀመረቸዉ የ7/24 የልማት ትጋት እንዲሳካ፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረጉና ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል፡፡

በተለይም በከተማዋ አይነታቸውን እና ቅረፃቸዉን እየቀያየሩ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ህዝብን የሚያማርሩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ የማድረጉ ስራ ትክሩት የሚሻ ነዉ ተብሏል፡፡

በቀጣይም የጋራ ትስስርን በመፍጠር ከተማዋን ወደ ከፍታ ማማ ለማሻገር እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ መስራት እንደሚገባም በዉይይቱ ተነስቷል፡፡

በሩዝሊን መሀመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review