በኦሮሚያ ክልል መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ተመላከተ

You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ተመላከተ

AMN – ግንቦት 23/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በትኩረት እንሰራለን ሲሉ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ለማልማት በትኩረት እየተሰራ አንደሚገኝ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፣ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶችም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የመሬት እና ኃይል አቅርቦት እንዲሁም ሌሎች ተግዳሮቶችን ለመፍታት ይሰራል ያሉት አቶ ሽመል፣ ባለሃብቶች እና አልሚዎች በክልሉ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኦሮሚያ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ በተለያዩ አካባቢዎች ያከናወናቸው ሥራዎች የሚበረታቱ እና አርአያ እንደሚሆኑ ያነሱት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያን በጠንካራ ኢኮኖሚ ላይ ለመገንባት በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

ባለሃብቶችም ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በልማት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ መንግስትም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የኢቨስትመንት አማራጮችን ለባለሃብቶች ለማስተዋወቅ ያለመ የክልሉ ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review