አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ለሰራተኞቹ ያዘጋጀው ስፖርታዊ ፌስቲቫል ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጠናቋል።
በማጠቃለያው ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተሳተፉበት የማስ ስፖርት ተከናውኗል።
የእግርኳስ ፣ የሩጫ እና ገመድ ጉተታ ውድድሮች የስፖርታዊ ፌስቲቫሉ የመዝጊያ ድምቀቶች ሆነዋል።
በውድድሮቹ አሸናፊ የሆኑ ቡድኖች የተዘጋጀላቸውን ዋንጫ ከተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከአቶ ካሳሁን ጎንፋ እና በምክትል ስራ አስፈፃሚ ማዕረግ የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ከአቶ ጌታቸው ዳዲ እጅ ተቀብለዋል።
ሰራተኛው በስራው ውጤታማ እንዲሆን እና ማህበራዊ ግንኙነቱን እንዲያጠናክር ታስቦ የተዘጋጀው ስፖርታዊ ፌስቲቫል ቀጣይነት እንደሚኖረው ተመላክቷል።
በሸዋንግዛው ግርማ





See insights and ads
All reactions:
176176