አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የተቋሙ ሰራተኞች ስራቸውን በአርዓያነት እንዲወጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልጸዋል፡፡
ሰራተኞቹ የተቋማቸውን ግብ በተሻለ ሁኔታ አከናውነው እንደሀገር ለድምር ውጤት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ በስልጠና ብሎም የተሻለ ልምድ እንዲቀምሩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ይህንን ተከታታይ ተግባር መነሻ በማድረግ የተከናወነውን ተግባር ተከትሎ በየዘርፉ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሰራተኞች ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዕውቅናው የተበረከተላቸው ሰራተኞች ዕድሉን እንዲያገኙ ካስቻሉ መስፈርቶች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ከሙስናና ብልሹ አሰራር መጽዳት የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ዕውቅና የተሰጣቸው ሰራተኞችም ዕድሉ ለበለጠ ውጤት እንደሚያነሳሳቸው ተናግረዋል።