ጠንካራ ሀገረ መንግስትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የሲቪል ማህበራት ድርሻ የጎላ መሆኑ ተጠቆመ

You are currently viewing ጠንካራ ሀገረ መንግስትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የሲቪል ማህበራት ድርሻ የጎላ መሆኑ ተጠቆመ

AMN-ግንቦት 24/2017 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሲቪል ማህበራት ጋር የማጠቃለያ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ፤ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የሲቪል ማህበራት ድርሻ የጎላ መሆኑን አስተዋል፡፡

እንደሀገር የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት ለሲቪል ማህበራት መብትን የሚያጎናፅፍ ሕግ አውጥቶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የሲቪል ማህበራትም የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ጠንካራ ሀገረ መንግስትን ለመገንባት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይ የህብረብሔራዊነት ማሳያ በሆነችው አዲስ አበባ ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጠናክር ስርአትን ለመዘርጋት ገዢ ትርክትን በማስረፅ የሲቪል ማህበራት ድርሻ የጎላ መሆን እንዳለበት በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review