የፌደራል ተቋማት እና ማኅበራት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ

You are currently viewing የፌደራል ተቋማት እና ማኅበራት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ

AMN – ግንቦት 24/2017 ዓ.ም

የፌደራል ተቋማት እና ማኅበራት አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል፡፡

ተቋማቱ ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሦስት ቀናት በአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ላይ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

በዛሬው ዕለትም አጀንዳዎቻቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፣ ለምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ እና ኮሚሽነር አምባዬ ኡጋቶ (ዶ/ር) አስረክበዋል።

በምክክር መድረኩ በቡድን የተሰባሰቡት አጀንዳዎች ተጠቃልለው ለዋናው መድረክ ከቀረቡ በኋላ ነው ለኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ርክክብ የተደረገው::

በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ባለው የፌዴራል ተቋማት እና ማኅበራት የምክክር የአደንዳ ማሰባስብ ሂደት ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ የአጀንዳ ግብዓቶቹን ሲያደራጁ እና ሲያጠቃልሉ የነበሩት የየቡድኖቹ ሰብሳቢዎች እና ፀሐፊዎች ናቸው የአጀንዳ ግብዓቶቹን ለመድረኩ እያቀረቡት::

በቀረቡት የተጠቃለሉ የአጀንዳ ግብዓቶች ላይ ሀሳብ ተሰጥቶ ለምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳዎቹን አስረክበዋል::

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review