በብሔራዊ መረጃና ደህንት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክትን ለሱዳኑ ጄኔራል አብዱል ፈተህ አል ቡርሀን አቀረቡ።
መልዕክቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በፖርት ሱዳን አቅርበዋል።
በፖርት ሱዳን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የገለፁት የልዑኩ መሪ “ሱዳን ሰላም እና መረጋጋቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ኢትዮጵያ የማይናወጥ ድጋፏን እንደምትቀጥል” በአፅንኦት መግለጻቸውን ተናግረዋል።