ትራምፕ እና ኤሎን መስክ ወደ መረረ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው ተነገረ

You are currently viewing ትራምፕ እና ኤሎን መስክ ወደ መረረ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው ተነገረ

AMN – ግንቦት 29/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ባለፀጋው ኢሎን መስክ በይፋ ወደ መረረ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል።

በኢለን መስክ የመኪና አምራች ድርጅት ቴስላ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደረው አዲሱ የትራምፕ የበጀት ረቂቅ አዋጅን ተለትሎ በሁለቱ የቀድሞ አጋሮች መካከል በተነሳው ቅራኔ ትራምፕ ከመስክ ንግድ ጋር በተለይም ለስፔስ ኤክስ አስፈላጊ የሆኑ የመንግስት ውሎችን እንደሚያቋርጡ ዝተዋል።

“በበጀታችን በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ለመቆጠብ ቀላሉ መንገድ የኢሎንን የመንግስት ድጎማ እና ኮንትራቶች ማቋረጥ ነው” ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለጥፈዋል።

በምላሹም መስክ የትራምፕን ክስ እንዲነሳ በመጠየቅ እና አሜሪካ የጠፈር ተመራማሪዎችን አና ሌሎች አቅርቦቶችን ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ማእከል ለማድረስ በዋነኛነት የምትጠቀምበትን የድራጎን የጠፈር መንኩራኩር በጊዜ ጡረታ እንደሚያስወጣው ዝቷል።

በፆታዊ ጥቃት ወንጀል ተከሶ በነበረው ጄፍሪ ኤፕስታይን ያልተለቀቁ ፋይሎች ውስጥ የትራምፕ ስም መኖሩንም ያለማስረጃ በመጠቀስ ”ትልቁን ፈንጂ” መጣሉም ተነግሯል።

መስክ ለትራምፕ እና ለሪፐብሊካኖች ስጋት በሚሆን መልኩ ለፖለቲካ ተፎካካሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አቅም አንዳለው ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review