የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት “ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ከተማ አቀፍ መድረክ ላይ ተገኝተን ከኪነጥበብ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
ኪነጥበብ የሀገርና የትውልድ ግንባታ አምባ መሆኑን በመገንዘብ በከተማችን የምናከናውናቸው የለውጥ ስራዎች የኪነጥበብ ባለሞያዎችን ተሳትፎ ያረጋግጥ ዘንድ በትብብር ለመስራት የተዘጋጀ መድረክ ነዉ።
በዛሬው ዕለትም ከኪነጥበብ ማህበረሰብ ጋር ባደረግነው ውይይት በጥንካሬም ሆነ በክፍተት ባነሷቸዉን ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ላይ የተወያየን ሲሆን በቀጣይ በከተማችን ሁለንተናዊ ለውጦች ዙሪያ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራት ተግባብተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡