በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት አሸንፎ ስልጣን የያዘ ፓርቲ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ከሚለይባቸው መንገዶች መካካል አካታችነቱ፣ አሳታፊነቱ፣ ከብሄር ጽንፈኝነት የጸዳ መሆኑ፣ ለብሄራዊ ትርክት የሚተጋ፣ ለኢትዮጵያ ትልቁን ጥላ እና አቅም በመላበሱ እና በመሰብሰብ የሚያምን ፓርቲ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ የተረሱና ዳር የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ መሀል ያመጣ እና ለዴሞክራሲ ቀናኢ የሆነ ፓርቲ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመላክተዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፖርቲ አባላትን ወደ ስልጣን ያመጣ ፓርቲ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ደግሞ የእኔ የግል ውሳኔ ሳይሆን የብልጽግና ፓርቲ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡
ብልጽግና ተመስርቶ በሚድህበት ጊዜ በተደረገው ምርጫ፣ ሌሎች ብዙ ጊዜ ካደረጉ ፓርቲዎች የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገበ ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም ብልጽግና ለዴሞክራሲ ካለው ቀናኢነት በተጨማሪ ብዙ አባላት ያሉት እና አስደማሚ ጉልበት ከጀርባው የያዘ ፓርቲ መሆኑን አመላክተዋል፡፡