እስራኤል የቴህራን ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

You are currently viewing እስራኤል የቴህራን ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

AMN – ሰኔ 09/2017 ዓ.ም

እስራኤል ከቀጣይ ጥቃቶች በፊት ኢራናዊያኑ ዋና ከተማዋን ቴህራንን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የቴህራንን የአየር ክልል ተቆጣጥረናል ካሉ ከሰዓታት በኋላ የተሰማ ማስጠንቀቂያ ነው።

እስራኤል ከሰዓታት በኋላ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን የሚገኙ ወታደራዊ መዋቅሮችን ኢላማ ያደረገ የአየር ድብደባ እንደምትፈፅም አናዶሉ ዘግቧል።

ይህን ተከትሎ የእስራኤል ጦር የመንግስት ሚኒስትሮች እና የውጭ ኤምባሲዎች የሚገኙበትን አንድ የቴህራን አውራጃ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አዟል።

ከሰኞ ማለዳ ጀምሮ ከምድር ወደ አየር የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከምእራብ ኢራን ክፍል ወደ ቴህራን ሲጓዙ እንደነበር የእስራኤል ጦር አስታውቋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review