ልመናና ተረጂነትን በዘላቂነት ለማስቀረት የስራ ባህልን መቀየር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ

You are currently viewing ልመናና ተረጂነትን በዘላቂነት ለማስቀረት የስራ ባህልን መቀየር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ

AMN- ሰኔ 10/2017

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የማምረቻ ቦታዎች የምረቃና ጉብኝት መርሀግር እየተካሄደ ነው።

በመርሃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነና ሌሎችም የከተማና የክፍለ ከተማው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

እንደ ሀገር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ድህነትን እና ኋላ ቀርነትን ለማስቀረት የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርና እንዲሁም ሌሎች በርካታ ኢኒሼቲቮች መከናወናቸውን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በእነዚህም ተጨባጭ ለውጦች ስለመምጣታቸው ገልፀዋል።

ልመናና ተረጂነትን በዘላቂነት ለማስቀረት የስራ ባህልን መቀየር ቁልፍ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባው አንስተው በመዲናዋም ይህን ገቢራዊ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ክህሎት መር የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው፡፡ የስራ እድል ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎችም በቴክኒክና ሞያ ሰልጥነው ብቁ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በዛሬው ዕለት እየተመረቁ ከሚገኙት የልማት ሥራዎች መካከል አንዱ የሆነው የገላን የዶሮ ክላስተር ሁሉም መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት ሲሆን ለሰባት ማህበራትም የስራ እድል የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review