የሚታየው ሁሉ ምድረ በዳ፣ ዙሪያውም ተራራ በሆነበት እጅግ ደረቅ በሆነ ወደር ባልተገኘለት ሃሩራማ በረሀ መሀል ጥም ይዝዎ በመንገላታት ላይ ሳሉ ድንገት ከአድማስ ዓይንዎት ዘመናዊውን ማቀዝቀዣ ቢመለከት ምን ሊሰማዎ ይችላል?
ነገሩ እንዲህ ነው ፤ በናሚቢያ የሚገኘው የናሚብ በረሀ መሀል በሃገሪቱ መንግስት የተቀመጠ ሃምራዊ ፍሪጅ ወይም ማቀዝቀዣ አለ።
ለዚያውም ከሚጠጣ ውሃ እና አረፍ ለማለት ታስበው ከተዘጋጁ ቅንጡ ወንበሮች ጋር።
በፀሀይ ሃይል የሚሰራው ማቀዝቀዣው በየጊዜው ንፅህናው እየተጠበቀ ይፀዳል፣ ጥራቱን የጠበቀ ውሃም ይቀመጥበታል።
ያንን ከባድ በረሃ አቋርጦ የሚሄድ ማንኛውም መንገደኛ ወይም በሌላ ምክንያት በዚያ የተገኘ ማንኛውም የተጠማ ሰው ፤ ከፍሪጁ እያወጣ በነፃ ጥሙን ይቆርጣል!! ይህም ለመንገደኞች እና በስፍራው ለተገኙ የሚደረግ አቀባበል ወይም ነፃ መስተንግዶ ነው።
ውሃው ሲያልቅም በአዲስ ይተካል።
መጀመሪያ አካባቢ ሰዎች ሃምራዊውን ፍሪጅ በጥርጣሬ ይመለከቱት ስለነበር ደፍረው አይከፍቱትም ነበር።
ይሁንና በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በኢንስታግራም በስፋት ከታየ በኋላ በርካቶች ከዓለም ዙሪያ ይህንን በበረሀ መሀል የተሰየመውን ተዓምር በአካል ለማየት ወደ ሥፍራው ያቀናሉ ሲል ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።
በማሬ ቃጦ