በመዲናዋ በዘንድሮር የክረምት ወቅት ውጤታማ የወንጀል መከላከል ስራ ለማከናወን በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

You are currently viewing በመዲናዋ በዘንድሮር የክረምት ወቅት ውጤታማ የወንጀል መከላከል ስራ ለማከናወን በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 10/2017 ዓ.ም

በዘንድሮር የክረምት ወቅት ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ ውጤታማ የወንጀል መከላከል ስራ ለማከናወን በትኩረት እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 የክረምት ወቅት የ90 ቀናት ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

የቀጣይ ዘጠና ቀናት እቅዶች ከመደበኛ ስራዎች በተጣጣመ አግባብ የተቀመጡና በልዩ ትኩረትና ቅልጥፍና ተፈጻሚ የሚሆኑ መሆኑን የገለጹት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ በክረምት ወቅት የሚጨምርብ የወንጀል ምጣኔን በተቀናጀ አግባብ መከላከል ይገባል ብለዋል።

በጠራ መረጃ ላይ የተመሰረተ የኦፕሬሽን ስራ ይሰራል ያሉት ኃላፊዋ፣ ማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን በማከናወን ህብረተሰቡ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህሉን የማጎልበት ስራ በቀጣይ 90 ቀናት በትኩረት የሚከናወን ይሆናል ብለዋል።

ጥራት ያለው የሰላም ሰራዊት ምልመላ ማከናወን ብሎም ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠርና የተቀናጀ የጸጥታ ስምሪትን ተግባራዊ በማድረግ የከተማዋን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ የመጠበቅ ተጨማሪ የቤት ስራ በክረምቱ ወቅት የሚወሰድ ይሆናልም ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በክረምቱ ተግባራዊ ለማድረግ የተቀመጡ እቅዶች ተፈጻሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በክረምቱ የከተማዋን ሰላም በተማሟላ አግባብ ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ሰው ተኮር የሆኑ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች በእቅዱ ተካተው ተግባራዊ እደሚደረጉ ተመላክቷል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review