ከንቲባ አዳነች አቤቤ በገባነው ቃል መሰረት ግልፅ መስፈርት አዉጥተን በመስፈርቱ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቁልፍ ርክክብ አድርገናል ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በገባነው ቃል መሰረት ግልፅ መስፈርት አዉጥተን በመስፈርቱ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቁልፍ ርክክብ አድርገናል ሲሉ ገለጹ

AMN ሰኔ 12/2017

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የንግዱን ማህበረሰብ እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ባወያየንበት ወቅት በቀረቡልን ጥያቄዎች መሰረት መልስ እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል።

አዲስ አባባ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም የሚሰራባት ከተማ እየሆነች ነው ።

ዛሬ ለአዲስና ለማስፋፊያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚቀርቡ የመስሪያ ቦታ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት ግልፅ መስፈርት አዉጥተን በመስፈርቱ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ አምራቾች ኢንዱስትሪዎች ቁልፍ ርክክብ አድርገናል ::

የመስሪያ ቦታ ቁልፍ የተረከባችሁ አርዓያ የሚሆን ስራ ሰርታችሁ ምርታማነትን በመጨመር እና የስራ እድል በመፍጠር ገበያን ማረጋጋት ይጠበቅባችኋል ፡፡

ያለንን መሬትና የሰው ሃይል ተጠቅመን በእልህ ስኬታማ እንሁን ፤ አምራቾችም ትልቅ ህልም ኖሯችሁ ዉጤታማ ሥራ ከእናንተ ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review