በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገርን እድገትና የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸዉን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ

You are currently viewing በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገርን እድገትና የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸዉን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN ሰኔ 12/2017

በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገርን እድገትና የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ።

ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በጎንደር ከተማ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በጎንደር ከተማ በፌደራልና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች የመፍታት አቅም መፍጠራቸዉን ተናግረዋል፡፡

ግንባታቸው እየተፋጠነ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሕዝቡና ከተማ አስተዳደሩ ተቀናጅተው የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሀገሪቱ የተውጣጡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ጉብኝት ትልቅ መነሳሳትንና ከተማዋን በስፋት ለማስተዋወቅና መልካም ገጽታዋንም ለማጉላት ምቹ አጋጣሚ የፈጠረ ነው ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮቹና አባላቱ በከተማው በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃውን የፒያሳ ኮሪደር ልማት ጨምሮ የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትና ጥገና ስራ እንዲሁም የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review