በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁለንተናዊ ልማቶች ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ፣ መሆናቸውን የአፍሪካ ህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ታዳሚዎች ገለጹ

You are currently viewing በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁለንተናዊ ልማቶች ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ፣ መሆናቸውን የአፍሪካ ህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ታዳሚዎች ገለጹ
  • Post category:ልማት

AMN – ሰኔ 14/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያከናወነ የሚገኘው ሁለንተናዊ ልማቶች ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ፣ የአከባቢ ጥበቃን ያስቀደሙ እና ለትውልድ ተሻጋሪ መሆናቸውን የአፍሪካ ህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ታዳሚዎች ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ላይ እየታደሙ ያሉ የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ተመራማሪዎች እና ለጋሾች የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ጎብኝተዋል።

ተሳታፊዎቹ የኮሪደር እና አጠቃላይ የከተማ መልሶ ማልማት፣ የአፍሪካ ነጻነት ምልክት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና የህጻናት ልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ለጋዜጠኞች አስተያየት የሰጡት ጎብኚዎቹ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያከናወነ የሚገኘው ሁለንተናዊ ልማቶች ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ፣ የአከባቢ ጥበቃን ያስቀደሙ እና ለትውልድ ተሻጋሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም በእያንዳንዱ የልማት ስራዎች ውስጥ ለህዝብ የጋራ ቦታዎች እና የነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህጻናት የተሰጠው ተጨባጭ ትኩረት ለሁሉም የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ አብነት ነው ማለታቸውን ከክንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review