የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀስላሴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአንጎላ ሉዋንዳ በይፋ ተከፍቷል።
የዘንድሮውን የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ፣ የትራምፕ አስተዳደር ድጋፍን መሰረት ካደረገው አሜሪካ አፍሪካን በተመለከተ የምትከተለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለመቀየር መወሰኑን ተከትሎ የሚካሄድ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።
በዚህ ጉባኤ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የሁለቱም ወገን የቢዝነስ መሪዎችን ጨምሮ 1 ሺህ 500 ተሳታፊዎች ታድመዋል።
ጉባኤው በአፍሪካና በአሜሪካ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችና እድሎች ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥም ታምኖበታል።
በጉባኤው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ስላሴ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ከዚህ ጎን ለጎንም የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶች የሚደርጉ ሲሆን፣ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ ቡድን አባላትም በጉባኤው በፓናል ውይይትና በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ነው ኢዜአ የዘገበው።