ከሕዝብ እና ከግል ሚዲያዎች የተወጣጡ ባለሞያዎች በጅማ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን እየጎበኙ ነዉ፡፡
የጅማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጅሃድ ሁሴን ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት ከሕዝብ እና ከግል ሚዲያዎች የተወጣጡ ባለሞያዎች ጅማ ከተማ ሲደርሱ በከተማዉ ከንቲባና በአካባቢዉ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎቹ በጅማ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ በእድሳት ላይ የሚገኘዉን የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስት መጎብኘታቸዉን ሃላፊዉ ተናግረዋል፡፡
ባለሙያዎቹ በልማት ምክንያት ለተነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች እየተገነቡ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በጅማ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንና የልማት ስራዎችን መመልከታቸዉን የጅማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጅሃድ ሁሴን ገልጸዋል፡፡
ከሕዝብ እና ከግል ሚዲያዎች የተወጣጡ ባለሞያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸዉ ይታወቃል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ