ኢትዮጵያ እና አንጎላ ያሏቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና አንጎላ ያሏቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

AMN ሰኔ 16/2017

ኢትዮጵያ እና አንጎላ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና ለማጎልበት ትብብሯቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከአንጎላው ፕሬዝዳንት እና ከወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር ጆ ሎሬንሶ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደው በአንጎላ ርዕሰ መዲና ሉዋንዳ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን ነው።

ሁለቱ መሪዎች የሀገራቱን ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ምቹ ሁኔታ ዙሪያ መምክራቸውን ውይይቱን የተከታተሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘርይሁን አበበ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በተለይም ግንኙነቱን ለማጠናከር ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ከግምት በማስገባት መሪዎቹ ከዚህ ቀደም በሁለቱ ሀገራት መካከል የተቋቋመው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚቴ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ መግባባት ላይ ደርሰዋል ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ በሁለቱም ወገን ያሉ ሚኒስትሮች መመሪያ እንዲሰጣቸው መነጋገራቸውንም እንዲሁ።

ሁለቱ መሪዎች በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላትን ሚና ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይም መመክራቸቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተቋማዊ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ መወያየታቸውንና አሁን ላይ ዓለም እያጋጠማት ላለው ችግር አፍሪካ መፍትሄ በማፈላለግ ግንባር ቀደም ሚና እንዲኖራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይም መክረዋል።

በመጨረሻም ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የአንጎላ መንግሥት ለኢትዮጵያ ልዑክ ላደረገው አቀባበል ለፕሬዝዳንት ሎ ሬንሶ ምስጋና ማቅረባቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review