የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይሆናል

You are currently viewing የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይሆናል

AMN ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንዳስታወቁት የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 3-4/2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት መሰጠቱን አስታዉሰዋል።

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተናዉ በአጭር ጊዜ ታርሞ መጠናቀቁን በመግለጽ ውጤቱ ዛሬ ይፋ ይሆናል ብለዋል።

ዉጤቱ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review