በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት ለማስቀጠል በተከናወኑ ቅንጅታዊ ሥራዎች የጥፋት ሀይሎችን ሴራና የንግድ አሻጥሮችን ማክሸፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት በ2017 በጀት አመት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በ2018 በጀት አመት ትኩረት ለደረግባቸው በሚገቡ ስራዎች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት በጋራ መስራት በመቻላቸው የጥፋት ሀይሎችን ሴራና የንግድ አሻጥሮችን ማክሸፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል።
በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) የከተሞችን ሰላም ለማስጠበቅ እና ያላቸውን እድገት ለማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አንስተው በሁለቱ ከተሞች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ለሚኖሩ ዜጎች ትስስር ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት ለማስቀጠል በተከናወነ ቅንጅታዊ ሥራ የተለያዩ የሽብርና ደረቅ ወንጀሎችን መከላከል እንደተቻለ በመድረኩ ተነስቷል።
አሸናፊ በላይ