የተዘጋን ኮሌጅ እናስከፍታለን ብለው ሲያጭበረብሩ የተደረሰባቸው ባለሙያዎችን ማባረሩን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለኤ ኤም ኤን አስታወቀ።
የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የተሰጠውን ስልጣንና ሃላፊነት ለመወጣት ባለስልጣኑ እየሠራ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዘዲን ሙስባህ ተነግረዋል።
አቶ ኢዘንዲን ከኤ ኤም ኤን ጋር ባዳረጉት ቆይታ ባለስልጣኑ ሙሉ በሙሉ ተግባሩን በቴክኖሎጂ ለማድረግ እየተጋ ባለበት በ2017 በጀት ዓመት 38 ባለሙያዎች ከሙያ ያፈነገጠ ተግባር ሲፈፅሙ ተደርሶባቸው የእርምት ርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል።
ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ ባለሙያዎች በሕግ አግባብ የተዘጋን ኮሌጅ እናስከፍታለን በማለት ሲያጭበረብሩ በጥቆማ ስለተደረሰባቸው ከስራ ገበታቸው መሰናበታቸውን ገልፀዋል።
በሲሳይ ንብረቱ