ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተፈጥሮና ማህበራዊ ህይወት መስተጋብር የፈጠሩበት ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው

You are currently viewing ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተፈጥሮና ማህበራዊ ህይወት መስተጋብር የፈጠሩበት ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው
  • Post category:ልማት

AMN ሰኔ 17/2017

ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ተፈጥሮና ማህበራ ዊ ህይወት መስተጋብር የፈጠሩበት ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው ሲሉ የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ።

የመገናኛ ብዙሃን በመንግስት የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ረገድ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡

ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ የህዝብ እና የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸዉ ይታወቃል፡፡

ከውይይቱ በኋላ ባለሙያዎቹ የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝምን ጎብኝተዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መንግሥት ከለያቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ ቱሪዝም ነው።

በዚህም ሁለት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየተሰራ እንዳለ ተናግረው፤ የመጀመሪያው ነባር ቅርሶችን የማደስ እና አዳዲስ መዳረሻዎችን ማልማት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው፥ አሁን ላይ የተሟላ የኢኮ ቱሪዝም ማዕከል መሆን መቻሉን እና ኢኮ ቱሪዝሙ ተፈጥሮና ማህበራዊ ህይወት መስተጋብር የፈጠሩበት ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው ብለዋል።

ሁለተኛው ኮንፍረንስ ቱሪዝም ላይ በትኩረት መስራት እንደሆነ አንስተው በዚህ ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።

ባለፉት ጊዜያትም በርካታ የኮንፍረንስ ቱሪዝም በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች መካሄዳቸውን ተናግረዋል።

ነባር መዳረሻዎችን ማደስና አዳዲስ መዳረሻዎችን መገንባት እንዲሁም ለኮንፍረንስ ቱሪዝም የተሰጠው ትኩረት ቱሪዝም እንዲያድግ ማድረጉን ገልጸዋል። በዚህም ከአመት አመት የቱሪስት ፍሰቱ እያደገ መምጣቱን መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እነዚህን አካባቢዎች አሁን ካለው የበለጠ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑ እና የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስገኙ የመገናኛ ብዙሃን መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ረገድ ኃላፊነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review