ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች በጎንደር ከተማ በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል

You are currently viewing ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች በጎንደር ከተማ በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል
  • Post category:ልማት

AMN ሰኔ 17/2017

በዚህ ወቅት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ፤ መንግስት ሰላምን ከማፅናቱ ጎን ለጎን ልማትን በፍጥነት ማስፈጸም እንደሚቻል በመላ ሀገሪቱ እየተካሄዱ የሚገኙ የኮሪደር ልማትና ከተማ የማስዋብ ፕሮጀክቶች አመላካቾች እንደሆኑ ገልጸዋል።

ጎንደር የቀደመ ስሟንና ዝናዋን የሚመጥን የልማት ተቋዳሽ ሳትሆን ለዘመናት መቆየቷን አስታውሰው፤ አሁን ላይ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማዋና አካባቢዋ እየተገነቡ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ወደ ቀደም ክብሩዋ የሚመልሱ ናቸው ብለዋል፡፡

የከተማዋን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ ላለፉት 17 ዓመታት ግንባታው ሲጓተት ቆየቶ ኋላም ቆሞ የነበረው የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ዳግም ግንባታው መጀመር የመንግስትን የማስፈጸም አቅም፣ ብቃትና ቁርጠኝነት ያመላከተ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሀገራችን የብዝሃ ታሪክና የስልጣኔ መገለጫ የሆነው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት እድሳትና ጥገና ስራም መንግስት ታሪክን ጠብቆና ተከባክቦ ለትውልድ ለማሻገር ያለውን ቁርጠኛ አቋም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

”ሕዝቡ ልማቱን በመደገፍ እያሳየው ያለው ትብብርና ተሳትፎ ጎንደር ላይ በተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራዎች ማረጋገጥ ችለናል” ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል።

ጎንደር ሰላሙዋንም ልማቱዋንም በአጭር ጊዜ ያረጋገጠች ከተማ መሆኑዋን አውስተው፤ ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ጎዳና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉ የልማት ስራዎች በከተሞቻችን እየታየ ነው ብለዋል፡፡

የሚዲያና ኮሙኒክሽን ባለሙያዎችና አመራሮች በሀገሪቱ እየተመዘገቡ ያሉ የለውጥና የልማት ስራዎችን ተከታትሎ በመዘገብ ለሌሎች ተሞክሮዎች እንዲሆን በትጋት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

”የጎንደር ከተማ ሕዝብ የኮሪደር ልማቱን በመደገፍ የልማት አሻራውን አሳርፏል” ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ናቸው፡፡

ይህም ህንጻና መኖሪያ ቤቱን በማደስና በማስዋብ እንዲሁም ቀለም በመቀባትና መብራት በመዘርጋት ጭምር እንደሆነ መጥቀሳቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና አመራሮቹ የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክትን ጨምሮ የከተማውን የኮሪደር ልማት እንዲሁም የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት የጥገናና የእድሳት ስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review