መንግስት ለሚዲያው መጠናከር ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing መንግስት ለሚዲያው መጠናከር ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN ሰኔ 18/2017

መንግስት ሚዲያውን ለማጠናከር ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ እና የግል ሚዲያዎች ከተወጣጡ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግስት የህትመት ሚዲያው እንዲጠናከር መደገፍ እንዳለበት ገልጸው መንግስት እና የግል ባለሀብቱ የወረቀት ኢንዱስትሪዎች በመክፈት ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ጅምር ስራዎች አሉ ብለዋል።

የህትመት ሚዲያው ላይ የወረቀት አቅርቦት ችግር እንዲፈታ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፋይናንስን በሚመለከት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ መንግስት ሚዲያዎች እንዳላቸው ባህሪይ እና የይዘት ስራ ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

ከመረጃ ስርጭት ጋር በተገናኘም መረጃዎች በወቅቱ ተደራሽ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህንን ለማጠናከር አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።

መንግስት ሚዲያው ዘላቂ የፋይናንስ አቅሙን በማረጋገጥ መርህ ላይ ቆሞ እንዲሰራ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review