የህዝባችንን ጥያቄዎች የምንመልሰዉ የሚታዩ ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነዉ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing የህዝባችንን ጥያቄዎች የምንመልሰዉ የሚታዩ ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነዉ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN ሰኔ 17/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነቸ አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የህዝባችንን ጥያቄዎች የምንመልሰዉ የሚታዩ ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነዉ ብለዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የኢንዱስትሪ ክላስተር ጎብኝተናል። 93 ሄክተር መሬት በመመደብ በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ ያለዉ ይህ የኢንዱስትሪ መንደር የመጀመሪዉ ምዕራፍ ከ120 በላይ ሼዶችን ያሉት እነዚህም ሲሆን ለብረታብረት ሥራ፣ ለእንጨት ውጤቶች፤ ለጨርቃ ጨርቅ ፣ ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣ የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸዉ።

ይህ ግዙፍ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ፤ የመስሪ ቦታ ችግርን ከማቃለል ባሻገር የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት፣ ሰፊ የስራ ዕድልን ለመፍጠር የኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው። የግብታው ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች የሚሆኑ ሼዶችን የያዘ ነው።

ይህ የኢንዱስትሪ መንደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሼዶች በተለየ ሁኔታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግብአቶችን እንዲጠቀም ተደርጎ እየተገነባ ነዉ።

በተጨማሪም ከቦሌ ኤርፖርት በጥቂት ደቂቃ መድረስ የሚያስችል አዲሱ የአቃቂ ቦሌ ካርጎ መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምርት ማጓጓዝን ታሳቢ ያደረገ እና ስትራቴጂክ ስፍራ ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው። አዲስ አበባን የኢትዮዽያ ብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review