ሩሲያ እና ማሊ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing ሩሲያ እና ማሊ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- ሰኔ 18/2017 ዓ.ም

ግንኙነታቸው እየተጠናከረ የመጣው ሩሲያ እና ማሊ የንግድ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ማሊና ሩሲያ የጋራ ንግድን ለማጎልበትና የኢኮኖሚ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ከእነዚህም መካከል በክሬምሊን በዝርዝር እንደተገለጸው በኒውክሌር ኃይል መስክ የበለጠ ትብብር ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ ላይ መድረስ ይገኙበታል።

ስምምነቶቹ ይፋ የተደረጉትም የማሊ መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ሞስኮን እየጎበኙ በነበረበት ወቅት ነው።

ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሁለት ሰዓታት የዘለቀ ውይይት ማካሄዳቸውም ተገልጿል።

ጎይታ በፈረንጆቹ 2021 ስልጣን ከያዙ በኋላ፣ ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ሲጠናከር ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ፈረንሳይ ጋር ያላቸው ግንኙነት ግን እየቀነሰ መምጣቱን የሩሲያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ጎረቤት ሀገር ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀርም ትብብር ከመሰረቱ በኋላ፣ ከሩሲያ ጋር ይበልጥ በመቀራረብ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በሰጡት አስተያየት፣ ምንም እንኳን ከማሊ ጋር ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ መጠነኛ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚመጣ ገልጸዋል፡፡

ወደፊት የሚደረገው ትብብር በስነ ምድር ምርምር፣ በኃይል፣ በሎጂስቲክስ እና በሰብዓዊ መስክ ያተኩራልም ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review