ኢትዮጵያ የፀጥታና ደህንነት ተቋሞቿን ለማዘመን እየሰራችው ያለው ሥራ ለሌሎች አገራት አርአያ እንደሚሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የፀጥታና ደህንነት ተቋሞቿን ለማዘመን እየሰራችው ያለው ሥራ ለሌሎች አገራት አርአያ እንደሚሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ

AMN – ሰኔ 18/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በዚሁ ውይይትም ከፍተኛ ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በልዩ ልዩ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያለውን ከፍተኛ ብቃትና መልካም አፈፃፀም እንደሚያደንቁ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የፀጥታና ደህንነት ተቋሞቿን ለማዘመን እየሰራች ያለው ሥራ ለሌሎች አገራትም አርአያ የሚሆን ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ልዩ ልዩ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆናቸውንና በዘርፉ በሚከናወኑ ሌሎች ተግባራትም ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ኢትዮጵያም ከኮሚሽኑ ጋር በተለይም በአቅም ግንባታና ስልጠና ዘርፎች አብራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት መጠቆማቸውን ከሚኒስትሯ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review