በቀጣይ 90 ቀናት እንደ ከተማ 30 አዳዲስ ከፍተኛ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing በቀጣይ 90 ቀናት እንደ ከተማ 30 አዳዲስ ከፍተኛ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

AMN – ሰኔ 19/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር የጋራ ምክክር ተደርጓል።

በምክክሩ ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎቹ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በቀጣይ 90 ቀናት በሚከናወኑ የመፍትሄ ስራዎች የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ተጋላጭነታቸውን በማስወገድ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅና የህብረተሰቡን ተጋላጭነትም የመከላከል ስራ እንደሚሰራ የኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጥናት ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ደሲሳ ጦና ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል ፡፡

እየተጠናቀቀ ባለው 2017 በከተማዋ ለተለዩ 111 ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች መፍትሄ ለመስጠት ዕቅድ ተይዞ የተሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ከዕቅድ በላይ 170 አካባቢዎች ላይ መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review