የኔቶ አባል ሃገራት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለወራት ጫና ሲያሳድሩበት የነበረውን የህብረቱን የመከላከያ በጀት ወደ 5 በመቶ ከፍ በኔዘርላንድ ሄግ ተገናኝተዋል።
በስብሰባው የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት፤ አሜሪካ ለረዥም ጊዜያት ከፍተኛውን ጫና ተሸክማ መቆየቷን አወድሰው የአውሮፓ ሃገራት ለመከላከያ በጀት የበለጠ ሀላፊነት የሚወስዱበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።
በርካታ መሪዎች ታሪካዊ ነው ባሉት በዚህ ስብሰባ የሚወሰነው ውሳኔ፤ የሰላም ጥሪው እንዳለ ሆኖ ለዩክሬን የሚደረገውን ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚያካትትም ዋና ፀሃፊው አስታውቀዋል።
አብዛኛዎቹ ሃገራት እ.ኤ.አ በ2035 ይደረስበታል በተባለው የ3.5 በመቶ የመከላከያ በጀት ግብ የተስማሙ ሲሆን ስፔን ባለመስማማት ውድቅ ማድረጓን ቢቢሲ ዘግቧል።
እንደ ቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር ያሉ አንዳንድ መሪዎች ደግሞ አዲሱ ግብ ከባድ ቢሆንም በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ተጨባጭ መሆን የሚችል ነው ብለዋል ።
ከ2019 በሗላ በዚህ ጉባኤ ሲገኙ የመጀመሪያቸው የሆነው ትራምፕ ከዩክሬን ይልቅ ስለ መካከለኛው ምስራቅ የበለጠ አፅንኦት ሰጥተው፤ በህብረቱ የጋራ መከላከያ ዋስትና ጉዳይ ስለሰፈረው የኔቶ አንቀጽ አምስት የመከላከያ ህግ ግልጽ ያልሆኑ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
በሊያት ካሳሁን