የአዲስ አበባ ሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጣቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንዲችሉ ሰልጣኞች ያላቸዉ አበርክቶ የጎላ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጣቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንዲችሉ ሰልጣኞች ያላቸዉ አበርክቶ የጎላ መሆኑ ተገለጸ

AMN-ሰኔ 19/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጣቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንዲችሉ ሰልጣኞች ያላቸዉ አበርክቶ የጎላ እንደሆነ ሂሩት ካሳዉ (ዶ/ር) ተናገሩ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ከስራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ 1 ሺህ 900 ሰልጣኞችን አስመርቀዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳዉ (ዶ/ር) አዲስ አበባ የተለያዩ ዲፕሎማቶች እና አምባሳደሮች መቀመጫ እንደመሆኗ በሆቴል ዘርፉ ላይ አበክሮ መስራት ይገባል ብለዋል።

በዛሬዉ ዕለት በሆቴል ማኔጅመንት ፣ በምግብ ዝግጅት ፣ በእንግዳ አቀባበል ፣ በመስተንግዶ እና በቤት አያያዝ በአጠቃላይ በአምስት ዘርፎች የሰለጠኑ ሰልጣኞች ተመርቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጣቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንዲችሉ የራሳቸውን አበርክቶ ማኖር እንደሚገባቸው ተመላክቷል፡፡

በትባረክ ኢሳያስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review