የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን እያስጎበኘ ይገኛል

You are currently viewing የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን እያስጎበኘ ይገኛል
  • Post category:ልማት

AMN ሰኔ 19/2017 ዓ.ም

በጉብኝቱ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ከዞን እና ከወረዳ የተውጣጡ ዳኞች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው በአጠቃላይ ከ500 በላይ የሚሆኑ ጎብኝዎች ተሳትፈዋል።

የኦሮሚያ ኪነጥበብ ማዕከል፣ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

በከተማዋ የተሰሩ እነዚህ ፕሮጀክቶች የኦሮሞን ባህልን እና እሴትን ለቀሪው አለም ከማስተዋወቅ ባለፈ የከተማዋን የቱሪዝም ዘርፍ የሚያበረታቱና የሚያስተዋዉቁ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review