የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት 34 ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ማከናወኑን ገለጸ

You are currently viewing የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት 34 ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ማከናወኑን ገለጸ
  • Post category:ልማት

AMN- ሰኔ 19/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት 34 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የጠጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ማከናወኑን ገልጿል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እንደገለጹት፣ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ግዙፍ እና ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ-ልማት ከመገንባት ጎን ለጎን የጠጠር መንገድ ጥገናና ግንባታዎችንም እያከናወነ ነው፡፡

በዚህም የከተማዋን ነዋሪዎች የመግቢያና መውጫ የመንገድ ችግር ለማቃለል በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች የመንገድ መሠረተ ልማት እያከናወነ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በጠጠር ደረጃ የመግቢያና መውጫ መንገድ ግንባታ ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ ስፍራዎች መካከል፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ውሃ ልማት ልዩ ስሙ ሰላም ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የአክሰስ መንገድ የሚጠቀስ መሆኑንም አቶ እያሱ ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት 34 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የጠጠር መንገድ ግንባታና ጥገና በራስ አቅም ገንብቷል ያሉት ኃላፊው፣ የጠጠር መንገድ ግንባታው በአጠቃላይ 700 ሜትር ርዝመት እና 10.5 ሜትር የጎን ስፋ የሚሸፍን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በሂሩት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review