በአፋር ክልል ኪልባቲ ራሱ በራህሌ ወረዳ የተከሰተውን ሰደድ እሳት 90 በመቶ መቆጣጠር መቻሉ ተገለጸ

You are currently viewing በአፋር ክልል ኪልባቲ ራሱ በራህሌ ወረዳ የተከሰተውን ሰደድ እሳት 90 በመቶ መቆጣጠር መቻሉ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 19/2017 ዓ.ም

በአፋር ክልል ኪልባቲ ራሱ በራህሌ ወረዳ በቡሬ ቀበሌ የተከሰተውን ሰደድ እሳት በህብረተሰቡ ጥረት 90 በመቶ የሚሆነውን መቆጣጠር እንደተቻለ የወረዳው አስተዳደሪ አቶ አሊ ሁሴን ገልጸዋል፡፡

በሰደድ እሳቱ እስከ አሁን ከ86 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የሚገኝ ጫካ መቃጠሉም ተነግሯል፡፡

በአካባቢው የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመከላከል የአካባቢው ማህበረሰብና መንግስት በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን የወረዳው አስተዳደሪ ተናግረዋል።

በትናንትናው እለት ከቀኑ 5 ሰአት ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ፣ 86 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ጫካ ማውደሙንና በአሁኑ ወቅትም በቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑን ተናግረዋል።

በአካባቢው ምቹ መንገድ አለመኖር እና የውሃ እጥረት እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አዳጋች እንዳደረጉትም ነው አቶ አሊ ሁሴን የገለጹት።

እስካሁንም 90 በመቶ የሚሆነውን የእሳት አደጋ በህብረተሰቡ ጥረት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል።

በአካባቢው ካለው ነፋስ የተነሳም በጫካው ላይ የበለጠ ጉዳት ሊደርስ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩንም አስረድተዋል።

በአብዱ መሀመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review