ለሐምሌ የተያዘው የከፍተኛ ታሪፍ ቀነ ገደብ ሊራዘም እንደሚችል ነጩ ቤተ-መንግስት አስታወቀ

You are currently viewing ለሐምሌ የተያዘው የከፍተኛ ታሪፍ ቀነ ገደብ ሊራዘም እንደሚችል ነጩ ቤተ-መንግስት አስታወቀ

AMN – ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሐምሌ ቀነ ገደብ የተያዘለትን በአውሮፓ ህብረት እቃዎች ላይ የሚጣለውን ከፍተኛ ቀረጥ ጊዜ ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ነጩ ቤተ-መንግስት አስታውቋል።

የፕሬዳንቱ የውሳኔ አዝማሚያ ቢታወቅም የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አለመደረሱን የገለፁት የቤተ-መንግስቱ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት፤ ምንም አይነት ስምምነት የማይደረግ ከሆነ ትራምፕ ለአሜሪካ ይጠቅማል ብለው የሚያስቡትን የታሪፍ ተመን ሊመርጡ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን የአውሮፓ ህብረት የቅርብ ጊዜውን የአሜሪካን ሀሳብ እየገመገመ እንደሆነ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ህብረቱ ለስምምነት ዝግጁ ቢሆንም አጥጋቢ ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ ማካካሻ ውሳኔዎችን በመወሰን የህብረቱን ፍላጎቶች እናስፈፅማለን ማለታቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል።

የአውሮፓ ኅብረት ቀድሞውኑ በብረት፣ በአሉሚኒየም፣ በመኪና እና በሌሎች ዕቃዎች ላይ ከአሜሪካ ከፍተኛ ታሪፍ ጋር እየታገለ እንደሆነ ያካተተው ዘገባው፤ አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ፈጣን ስምምነትን ሲጠይቁ አንዳንዶች ፍትሃዊ አይደለም ያሉትን የታሪፍ ተመን መንቀፋቸውን አካቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review