የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በአራቱም የባቡር መስመሮች በሰጠዉ አገልግሎት ከ270 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርሀን አበባው (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርሀን አበባው (ዶ/ር) በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እንደገለፁት ድርጅቱ በበጀት አመቱ በቀን 230 ፤በአመት 85 ሺህ 460 የባቡር ትራንስፖርት ምልልሶችን አድርጓል ፡፡
ድርጅቱ ባሳለፍነው በጀት አመት በ19 ባቡሮች ለ16 ሚሊየን 546 ሺህ 235 የከተማዋ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠቱን ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ በቀጣይ በጀት አመት ስራውን የበለጠ ለማሻሻል እንደሚሰራ የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚፈልጉ ተሳፋሪዎች ቲኬት ለማግኘት ወረፋ መያዝ ሳያስፈልጋቸው በቴሌ ብር ተጠቅመው ቲኬት መቁረጥና አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም አመልክተዋል፡፡
በሽመልስ ታደሰ