የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የሩሲያን ማዕቀብ ለ6 ወራት ለማራዘም ተስማሙ

You are currently viewing የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የሩሲያን ማዕቀብ ለ6 ወራት ለማራዘም ተስማሙ

AMN – ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የሩሲያ ወዳጅ ሃገር ሃንጋሪ ልታዘገየው ትችላለች የሚል ስጋት የነበረበትን የሩሲያ ማዕቀብ ለተጨማሪ 6 ወራት ለማራዘም ተስማምተዋል።

በብራስልስ የተካሄደው የህብረቱ ጉባኤ ከ200 ቢሊዮን ዩሮ በላይ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ንብረቶችን ማገድን ጨምሮ ሌሎችንም ቢያንስ እስከ 2026 ድረስ ፀንቶ እንዲቆይ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።

ይሁን እንጂ ስሎቫኪያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በሩሲያ ጋዝ ወደ ሀገር ውስጥ ስለማስገባት ባላት ውዝግብ ምክንያት አዲሶቹን ጥቅል ማዕቀቦችን ተቃውማለች።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በቪዲዮ በተላለፈ መልእክት የህብረቱ መሪዎች በሩሲያ የነዳጅ ንግድ፣ ባንኮች እና የጦር መሳሪያዎችን ለማምረት የሚረዱ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ላይ ያነጣጠረውን ማዕቀብ እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review